Copyright 2024 - Marathon Motor Engineering Ethiopia

የሥልጠናና የሥራ ቅጥር ማስታወቂያ

ሃገር በቀል የሆነው ኩባንያችን ማራቶን ሞተር ኢንጅነሪንግ ኃ/የተ/የግ/ማኅበር በዓለም ላይ በከፍተኛ ደረጃ ተመራጭና ዘመናዊ የሆኑትን የተለያዩ በጋዝና በኤሌክትሪክ የሚሰሩ የሃንዳይ ተሽከርካሪዎች ገጣጣሚና አከፋፋይ እንዲሁም ከፍተኛ መዋእለ ነዋይ በማፍሰስና በከፍተኛ ቴክኖሎጂ በመታገዝ በድህረ ሽያጭ ዘርፍም በተለያዩ ቅርንጫፎቹ ደረጃውን የጠበቀ የጥገና አገልግሎት እንዲሁም ኦሪጅናል መለዋወጫዎችን በማቅረብ ለደንበኞቹ የተሟላ አገልግሎት በመስጠት ላይ ሲሆን እንደ ሃገር በቀል ኩባንያ ቴክኖሎጂዎች፣ እውቀቶችና ክህሎቶች እንዲስፋፉና ለሃገራችን እንዲጠቅሙ እንዲሁም የተግባር እውቀትን በማስፋፋት ረገድ ሃገራችን ያለባትን ክፍተት ለማገዝ እንዲያስችል ኩባንያችን ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ በተከታታይ ላለፉት ዓመታት ምሩቃንን እየተቀበለና እያሰለጠነ በኩባንያው የሥራ እድል በመስጠት ከፊሉን ደግሞ ብቁና ተወዳዳሪ እንዲሆኑ በማድረግ ሃላፊነቱን በከፍተኛ ደረጃ እየተወጣ ያለ ኢትዮጽያዊ ኩባንያ ነው፡፡ በዚህም በጀት ዓመት የመጀመሪያ ዙር የሆኑትን የዩኒቨርሲቲና የኮሌጅ ምሩቃንን በመቀበል የኪስ ገንዘብ እየከፈለ በኩባንያው ውስጥ የስራ ላይ ስልጠና በመስጠትና በማብቃት በኩባንያው ውስጥ ለመቅጠር ከፊሉን ደግሞ አብቅቶ ስልጠናውን በሚወስዱበት መስክ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ የምንግዜም እቅዱ የሆነው ኩባንያችን በሚከተሉት የሥራ መስኮች ሰልጣኞችን አወዳድሮ ለመቀበልና ለማሰልጠን ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም ከዚህ በታች የተገለጸው የትምህርት መስክና የትምህርት ደረጃ ያላችሁ፣ ባለፈውና በያዝነው  ዓመት የተመረቃችሁ አመልካቾች ተጋብዛችኋል፡፡ይህ ስልጠና ከዚህ በፊት የስልጠና እድሉን ላላገኙት እድሉን ለመስጠት የታሰበ ሲሆን ከዚህ በፊት በትምህርት መስኩ በኩባንያችንም ሆነ በሌላ ተቋም ምንም አይነት ስልጠና የወሰዱትን ወይንም ስራ ያላቸውን አይመለከትም፡፡

ስልጠናው የሚሰጠው እዚሁ በአዲስ አበባ ኩባንያው ባሉት የስራ ቦታዎች ሲሆን ልዩ ክህሎት ያላቸው ምሩቃን ይበረታታሉ፡፡         

ተ.ቁ.

የትምህርት መስክ

የትምህርት ደረጃ

ብዛት

1

Automotive /Mechanical Engineering

Bsc. Degree

 

8

2

Industrial Engineering

Bsc. Degree

2

3

Hardware Engineering

Bsc. Degree

2

4

Software Engineering

Bsc. Degree

2

5

Marketing Management

 

BA degree

4

6

Business Management

BA degree

3

7

Accounting & Finance

BA Degree

5

8

Law

BA Degree

1

9

Auto Engine Servicing

Level 3 & 4

35

10

Auto Electrical/Electronic servicing

Level 3 & 4

10

11

GMF

Level  3& 4

15

12

Accounting

Level 3& 4

7

 

በመሆኑም ከዚህ በላይ የተገለጸውን የምታሟሉ አመልካቾች የትምህርት ማስረጃችሁን ኦሪጅናልና ኮፒውን በመያዝ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 8 (ስምንት) ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ሳሪስ በሚገኘው የኩባንያው ዋና መ/ቤት የሰው ሃይል አስተዳደር ቢሮ  ምድር ቤት በአካል በመገኘት ማመልከት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

ማሳሰቢያ፡ በዲጂታል መልእክት ማስተላለፊዎች የሚላኩ ማመልከቻዎች ተቀባይነት አይኖራቸውም፡፡

 ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁ.  251-11-4-70-92-71

ማራቶን ሞተር ኢንጂነሪንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር

ሳሪስ ዋናው መ/ቤት

አዲስ አበባ ፣ ኢትዮጽያ

 የማመልከቻ ማብቂያ ቀን ጥር 20 /2014 ዓ.ም

Comments powered by CComment

f t m

Contact Us

Head Quarter: Saris

Phone: +251 114 707 322

Fax: +251 114 709 940

whoIsOnline

We have 42 guests and no members online